About Us
ድርጅታችን ከኢትዮጵያ ምን እንታዘዝ ከተቋቋመት ከ2022 ጀምሮ በአሜሪካ ፣ በካናዳ እና አውሮፓ ለደንበኞቻችን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን እየሰጠን እንገኛለን። የምንሰጣቸው አገልግሎቶች የኢትዮጵያ የባልትና ውጤቶችን ፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ አልባሳት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጻህፍት እና ንዋየ ቅዱሳት፣ ኢትዮጵያን የሚያስተዋውቁ የተለያዩ የህትመት ውጤቶች ፣ የኢትዮጵያ ብሔብሔረሰቦች ባህላዊ መገልገያ እቃዎች አና የሙዚቃ መሳሪያዎች፣ የብራና ስዕሎችና ፅሁፎች ፣ የዕደ–ጥበብ ውጤቶች ባሉበት ሀገር እንልካለን። ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚተገበሩ የተለያዩ ፖሮጀክቶችን ማማከር እንዲሁም የፖሮጀክቶችን የአፈፃፀምየ ሂደቶችን መከታተልና በማስፈፀም ለባለቤቱ የማስረከብ ስራዎችን እንተገብራለን።
ራዕይ
በአለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያ ባህልና ዕሴት ትውፊት እንዲታወቅ ማድረግ።
ተልዕኮ
ባታና ጊዜ ሳይገድበን ከሀገር ውጪ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ምርቶችን እና ኢትዮጵያ ውስጥ የሚተገበሩ ኢንቨስትመንቶችን እውን እንዲሆ ማድረግ።
ግብ
እንደሚታወቀው ሁሉ የኢትዮጵያ ውጤቶች በአለማቀፍ ደረጃ ገበያ ላይ በብዛት አይገኙም። ይህንን ችግር ለመቅረፍ ድርጅታችን የተለያዩ እቅዶችን ነድፎ እየተገበረ ይገኛል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ግቦች አውጥተን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን።
- ፩) HASP መርሆችን በመተግበር ጤንነቱ የተረጋገጠ የባልትና ውጤቶችን ተደራሽ ማድረግ፣
- ፪) ኢትዮጵያ ውስጥ የሚተገበሩ ኢንቨስትመንቶችን በተለያየ ዘርፍ እገዛ ማድረግ
- ፫) ድርጅታች የተለያዩ ማህበራዊ ድህረገፆችን በመጠቀም የኢትዮጵያን ምርቶችን በማስተዋወቅ ለኢትዮጵያውያን ተደራሽ ማድረግ
የድርጅታችን አደረጃጀት
ድርጅታችን ስድስት ቋሚ ሰራተኞች እና አራት ጊዜያዊ ሰራተኞች አሉት። በቢሮ ደረጃ የሚከተሉት ተገልፀዋል።
፩) ኪሩቤል ደርቤ (ዶ/ር) (DVM)
• የድርጅቱ መስራች እና ስራ አስኪያጅ
• የ DYK kids fashion and design መስራች እና ባለቤት
• የ 12 አመታት በተለያዩ የኢንቨስትመት ስራዎች የማማከር ልምድ ያላቸው
፪) ወ/ሮ አበበች ከበደ
• ከ 30 አመታት በላይ የባልትና ውጤቶችን የማዘጋጀት ልምድ ያላቸው
• በተለያዩ ፖሮግራሞች ማለትም ሠርግ ፣ ቀለበት ፣ ክርስትና እና የራት ግብዣዎች የመደገስ የካበተ ልምድ ያላቸው
፫) ወ/ት ቢታኒያ ደርቤ
• በፋርማሲ እና በቢዝነስ ማኔጅመት የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው
• የድርጅታችን የባልትና ውጤቶች ደህንነት ተቆጣጣሪ እንዲሁም የግብይት ሀላፊ